👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን!!!!! የውዷ እህቴ (የአልሚና)ፀሀይ በድንገት ጠለቀች!!! SUN RISE 1947-SUN SET JUNE-15 – 2020.የእናቴ ምትክ ውዷ ሁልግዜ እየናፈቁሽ ሳንገናኝ ለተሰናበትሽኝ ውዷ ፣እህቴ የአልማዝ አረጋ አጭር የህይወት ታሪክ።አልማዝ አረጋ ከአባቷ ከአቶ ጥላሁን ዳምጤ እና ከእናቷ ከወይዘሮ አጥናፌወርቅ ይልማ በ1947 አመተምህረት በአዲስ አበባ፣ተወለደች ።ወይዘሮ አልማዝ ትምህርቷን በቀድሞው አስፋወሰን ትምህርት ቤት ተከታትላለች።ከዝያም ከአቶ በላይነህ ተክለ ወልድ ጋር በህግ ተጋብተው 8 ልጆችና ከ13በላይ የልጅ ልጆች አይታለች።ወይዘሮ አልማዝ አረጋ በድንገተኛ የልብ ህመም በተወለድ ፣በ73 አመታችው ፣ዘላለም ወደምትናፍቀው አምላክን ፈጣሪዋ፣ጥሪዋ ደርሶ አንቀላፍታለች።ወይዘሮ አልማዝ አመለ ሸጋ፣ልጆቿን፣የልጅልጆቿን ስብስባ እስከ ህይወቷ፣ፍፃሜ ድረስ የእናትነት ፍቅሯን የለገሰች ፣እንደ እናት፣የልጆቿንፍቅር ያልጠገበች፣አመለሸጋ መልካም እናት ነበረች።አልሚና ደጓ፣ እህቴ አሜሪካን፣እኔ ጋር በነበርሽ ግዜ፣ያሳለፍነውን ብርቅ ግዜ በህይወት ያጣናትን እናታችን ጎዶሎውን ቦታ የሞላሽበትን ፣ዘወትር በትዝታ እናስታውሰዋለን።እንግዲህ ምን እንላለን፣እግዝአብሄር የወደደውን ያደርጋል።ለእህቶቿ፣ለወንድሞቻ፣ለልጆቿና፣ለልጅ ልጆቿ፣መፅናናትን፣እንመኛለን።እሌኒ ወልዴ ፣ብዙነሽ ወልዴ፣አጥናፈወርቅ አረጋ፣ሜላት አረጋ እና ወንድሞች መስፍን እና ፋሲል አረጋ ለመላው ቤተሰብ መፅናናትን፣እንመኛለን።👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏